የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች icon

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

★★★★★
★★★★★
(4.53/5)

23.02Free8 months ago

Download የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች APK latest version Free for Android

Version 23.02
Update
Size 13.91 MB (14,587,906 bytes)
Developer Apps Show
Category Apps, Books & Reference
Package Name amharic_bible.ethiopian_bible_verses.share_bible
OS 4.1 and up

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች APPLICATION description

Bible verses. Read. Share. Namely through a new way to read the Bible
መጽሐፍ ቅዱስ ነብያትና ሓዋሪያት በመንፈስ ተመርተው የጻፉት የክርስቲያኖች እምነት መጽሓፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳንና በአዲስ ኪዳን ተከፍሎ 66 መጻሕፍት አሉት። ከነዲዩትሮካኖኒካል መጻሕፍትም ጋራ የመጻሕፍት ቁጥር 81 ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስ ምንነት

በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተለመደው «ባይብል» የሚለው ቃል ከጥንቱ የኮይነ ግሪክኛ ቋንቋ የተወሰደ ሲሆን ቃሉ የተገኘበት τὰ βιβλία /ታ ቢብሊያ/ የሚለው ሀረግ «መጽሐፍቱ» ወይም «ትንንሽ መጽሐፍት» ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። የዚሁም ቃል መነሻ ከግሪኩ ስም ΒύβλΠς /ቢውብሎስ/ (ፓፒሩስ ወይም ቄጠማ፣ የወረቀት ተክል) ሲሆን ይሄ ቃል «ፓፒሩስ» ከተነገደበት ከተማ ጌባል / ቢውብሎስ ስም መጣ።

መጽሐፍ ቅዱስ ለአይሁድና ክርስትና እምነት የእምነት መሰረት የሆኑ ትናንሽ መጽሐፍትን የያዘ አንድ ጥራዝ ነው። በተለምዶ «ብሉይ ኪዳን» በመባል የሚጠራውና በአይሁዳውያን በ24 እና በክርስቲያኖች በ39 መጽሐፍት የሚከፈለው የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ክፍል በመጀመሪያ በአብዛኛው የተጻፈው በጥንታዊው የዕብራይስጥ ቋንቋ ሲሆን የተጻፉበት ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት የተወሰኑ መቶ አመታት ቀደም ብሎ እንደሆነ ይነገራል። እነዚህን መጽሐፍት የጻፉት በወቅቱ የነበሩ የታመኑ አይሁዳውያን ወይም እስራኤላውያን ናቸው። የመጨረሻዎቹን 27 መጻሕፍት በግሪክኛ የጻፏቸው ክርስቲያኖች ሲሆኑ «አዲስ ኪዳን» በመባል በሰፊው ይታወቃሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ማስረጃም ሆነ በጣም ጥንታዊ የሆኑት ወጎች እንደሚጠቁሙት እነዚህ 66 መጻህፍት የተጻፉት ግብጽ ኃያል ከነበረችበት ጊዜ አንስቶ ሮም የዓለም ኃያል መንግስት እስከ ነበረችበት ዘመን ባሉት 1600 ዓመታት ውስጥ ነው።

በካቶሊክ ቤተክርስቲያን እምነት መሰረት ከ66ቱ መጽሐፍት በተጨማሪ የተካተቱ የተወሰኑ መጽሐፍት ሲኖሩ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እነዚህ ተጨማሪ መጻሕፍት (ዲዩቴሮካኖኒካል በመባልም ይታወቃሉ) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተካተቱትን መጻሕፍት ቁጥር ወደ 81 ያደርሱታል።

ከክርስቶስ ስብከት ቀጥሎ ምዕመናን የሆኑት ለረጅም ዘመን ተጨማሪ መጻሕፍቱን ከነመጽሐፈ ሄኖክና ኩፋሌ ያንብቡ ነበር። የአይሁድ ሰንሄድሪን ረቢዎች በ100 ዓ.ም. አካባቢ በተለይም ረቢ አኪቫ በን ዮሴፍ እነዚህን ተጨማሪ መጻሕፍት ከዕብራይስጥ ቅጂ አጠፉ። እስካሁንም ድረስ በዕብራይስጥ ትርጉም አይታወቁም። አዲስ ኪዳን ከተጻፈ በኋላ፣ ብዙ አጠያያቂ ወንጌሎችና የሌሎች እምነቶች ጽሑፎች ደግሞ ሊሠራጩ ጀመር። ግኖስቲክ የተባለው እምነት ተከታዮች በተለይ ብዙ ሥነ ጽሑፍ ፈጠሩ፣ ይህ ግን ከኦርቶዶክስ ወንጌል የተዛቡ ትምህርቶች ነበር። በ170 ዓ.ም. በክርስትያኖች ዘንድ የቱ መጻሕፍት ትክክለኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ናቸው? የሚል ጥያቄ ይነሣ ጀመር። መሊቶ ዘሳርዲስ የተባለ ጳጳስ በዚያን ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም መጻሕፍት ቤት ጉዞ አድርጎ የ ዕብራውያን መጻሕፍት ምን ምን እንደ ነበሩ ዘገበ። ተጨማሪ መጻሕፍቱ ከዚያ በፊት ስለ ጠፉ አልተዘገቡም። ስለዚህ ከዚህ በቀር ምንም ያልተዘረዘሩት ብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ትክክለኛ አይሆኑም የሚል ሀሣብ በሮሜ መንግሥት ክርስቲያኖች ተነሣ። ይህም የአይሁዶች ቀኖና በንቅያ ጉባኤ (317 ዓ.ም.) በሮሜ መንግሥት ለክርስቲያኖች ጸና።
↓ Read more
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 1 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 2 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 3 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 4 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 10 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 11 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 13 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች screen 16

Old versions

Version Size Update
⇢ 9.0 (1 variants) ↓ 3.10 MB ◴ 2 years ago
⇢ 6.0 (1 variants) ↓ 3.86 MB ◴ 4 years ago
⇢ 2.2 (1 variants) ↓ 2.93 MB ◴ 5 years ago